ኢዮብ 22:13-17 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

13. ይህም ሆኖ ሳለ እንዲህ አልህ፤ ‘እግዚአብሔር ምን ያውቃል?በእንዲህ ያለ ጨለማ ውስጥስ ይፈርዳልን?

14. በሰማይ ክበብ ላይ ሲራመድ፣እንዳያየን ጥቅጥቅ ያለ ደመና ይሸፍነዋል።’

15. ኀጢአተኞች በሄዱባት፣በጥንቷ መንገድ እንደ ተመላለስህ ትቀራለህን?

16. ጊዜያቸው ሳይደርስ ተነጠቁ፤መሠረታቸውም በጐርፍ ተወሰደ።

17. እግዚአብሔርንም ‘አትድረስብን!ሁሉን የሚችል አምላክም ምን ያደርግልናል?’ አሉ።

ኢዮብ 22