ኢዮብ 20:16-21 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

16. የእባብ መርዝ ይጠባል፤የእፉኝትም ምላስ ይገድለዋል።

17. ማርና ቅቤ በሚያፈሱ ጅረቶች፣በወንዞችም አይደሰትም።

18. የለፋበትን ሳይበላው ይመልሳል፤ከንግዱም ባገኘው ትርፍ አይደሰትም፤

19. ድኾችን በመጨቈን ባዶአስቀርቶአቸዋልና፣ ያልሠራውንም ቤት ነጥቆአል።

20. “ክፉ ምኞቱ ዕረፍት አይሰጠውምሀብቱም ሊያድነው አይችልም።

21. ያለውን አሟጦ ስለሚበላ፣ዘላቂ ብልጽግና አይኖረውም።

ኢዮብ 20