25. የሚቤዠኝ ሕያው እንደሆነ፣በመጨረሻም በምድር ላይ እንደሚቆም ዐውቃለሁ።
26. ቈዳዬ ቢጠፋም፣ከሥጋዬ ብለይም፣ እግዚአብሔርን አየዋለሁ፤
27. ሌላ ሳይሆን እኔው በገዛ ዐይኔ፣እኔ ራሴ አየዋለሁ፤ልቤ በውስጤ ምንኛ በጉጉት ዛለ!
28. “ ‘የችግሩ መንሥኤ በውስጡ አለ፤እኛ እንዴት እናሳድደዋለን?’ ብትሉ፣
29. ቍጣ በሰይፍ መቀጣትን ያስከትላልና፣ራሳችሁ ሰይፍን ፍሩ፤በዚያን ጊዜ ፍርድ እንዳለ ታውቃላችሁ።”