ኢዮብ 15:25-29 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

25. እጁን በእግዚአብሔር ላይ አንሥቶአልና፤ሁሉን የሚችለውን አምላክም ደፍሮአል፤

26. ወፍራምና ጠንካራ ጋሻ አንግቦ፣ሊቋቋመው ወጥቶአል።

27. “ፊቱ በስብ ቢሸፈን፣ሽንጡ በሥጋ ቢደነድንም፣

28. መኖሪያው በፈራረሱ ከተሞች፣የፍርስራሽ ክምር ለመሆን በተቃረቡ፣ሰው በማይኖርባቸው ወና ቤቶች ውስጥ ይሆናል።

29. ከእንግዲህ ባለጠጋ አይሆንም፤ ሀብቱም አይቈይም፤ይዞታውም በምድር ላይ አይሰፋም።

ኢዮብ 15