ኢዮብ 12:21-24 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

21. የተከበሩትን ውርደት ያከናንባል፤ብርቱዎችንም ትጥቅ ያስፈታል።

22. የጨለማን ጥልቅ ነገሮች ይገልጣል፤የሞትንም ጥላ ወደ ብርሃን ያወጣል።

23. ሕዝቦችን ታላቅ ያደርጋል፤ መልሶም ያጠፋቸዋል፤ሕዝቦችን ያበዛል፤ ያፈልሳቸዋልም።

24. የዓለም መሪዎችን ማስተዋል ይነሣል፤መንገድ በሌለበት በረሓም ያቅበዘብዛቸዋል፤

ኢዮብ 12