ኢዩኤል 2:3-6 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

3. በፊታቸው፣ እሳት ይባላል፤በኋላቸውም ነበልባል ይለበልባል፤በፊታቸው ምድሪቱ እንደ ዔድን ገነት ናት፤በኋላቸውም የሚቀረው ባዶ ምድረ በዳ ነው፤ምንም አያመልጣቸውም።

4. መልካቸው እንደ ፈረስ መልክ ነው፤እንደ ጦር ፈረስም ይጋልባሉ።

5. ገለባ እንደሚበላ እንደሚንጣጣ እሳት፣ለጦርነት እንደ ተዘጋጀ ኀያል ሰራዊት፣የሠረገሎችን ድምፅ የሚመስል ድምፅ እያሰሙ፣በተራሮች ጫፍ ላይ ይዘላሉ።

6. በእነርሱ ፊት ሕዝቦች ይርዳሉ፤የሁሉም ፊት ይገረጣል።

ኢዩኤል 2