ኢዩኤል 1:7-11 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

7. የወይን ቦታዬን ባድማ አደረገው፤የበለስ ዛፎቼንም ቈራረጠ፤ቅርንጫፎቻቸው ነጭ ሆነው እስኪታዩ ድረስ፣ቅርፊታቸውን ልጦ፣ወዲያ ጣላቸው።

8. የልጅነት እጮኛዋን እንዳጣች ድንግል፣ማቅ ለብሳችሁ አልቅሱ።

9. የእህል ቊርባንና የመጠጥ ቍርባን፣ ከእግዚአብሔር ቤት ተቋርጦአል፤ በእግዚአብሔርም ፊት የሚያገለግሉ፣ካህናት ያለቅሳሉ።

10. ዕርሻዎች ባዶአቸውን ቀርተዋል፤ምድሩም ደርቆአል፤እህሉ ጠፍቶአል፤አዲሱ የወይን ጠጅ አልቆአል፤ዘይቱም ተሟጦአል።

11. እናንት ገበሬዎች፣ ዕዘኑ፤እናንት የወይን ገበሬዎች፣ ዋይ በሉ፤ስለ ገብሱና ስለ ስንዴው አልቅሱ፤የዕርሻው መከር ጠፍቶአልና።

ኢዩኤል 1