ኢዩኤል 1:5-8 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

5. እናንት ሰካራሞች፤ ተነሡ፤ አልቅሱ፤እናንት የወይን ጠጅ ጠጪዎች ሁሉ፤ ዋይ በሉ፤ስለ አዲሱ የወይን ጠጅ ዋይ ብላችሁ አልቅሱ፤አፋችሁ ላይ እንዳለ ተነጥቃችኋልና።

6. ኀያልና ቊጥር ስፍር የሌለው ሕዝብ፣ምድሬን ወሮአታልና፤ጥርሱ እንደ አንበሳ ጥርስ፣መንጋጋውም እንደ እንስት አንበሳ መንጋጋ ነው።

7. የወይን ቦታዬን ባድማ አደረገው፤የበለስ ዛፎቼንም ቈራረጠ፤ቅርንጫፎቻቸው ነጭ ሆነው እስኪታዩ ድረስ፣ቅርፊታቸውን ልጦ፣ወዲያ ጣላቸው።

8. የልጅነት እጮኛዋን እንዳጣች ድንግል፣ማቅ ለብሳችሁ አልቅሱ።

ኢዩኤል 1