16. አብርሃም ባያውቀን፣እስራኤልም ባያስታውሰን እንኳ፣አንተ እኮ አባታችን ነህ፤ እግዚአብሔር ሆይ፤ አንተ አባታችን ነህ፤ከጥንትም ቢሆን ስምህ “ቤዛችን” ነው።
17. እግዚአብሔር ሆይ፤ ከመንገድህ እንድንወጣ፣ልባችንን በማደንደን ለምን እንዳንፈራህ አደረግኸን?ስለ ባሮችህ ስትል፣ስለ ርስትህ ነገዶች ስትል እባክህ ተመለስ።
18. ለጥቂት ጊዜ ሕዝብህ የተቀደሰውን ስፍራ ወርሶ ነበር፤አሁን ግን ጠላቶቻችን መቅደስህን ረገጡት።