ኢሳይያስ 59:17-19 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

17. ጽድቅን እንደ ጥሩር አጠለቀ፤የድነትን ቊር በራሱ ላይ ደፋ፤የበቀልንም ልብስ ለበሰ፤መጐናጸፊያ እንደሚደረብም ቅናትን ደረበ።

18. እንደ ሥራቸው መጠን፣ቊጣን ለባላጋራዎቹ፣ፍዳን ለጠላቶቹ፣እንደዚሁ ይከፍላቸዋል፤ለደሴቶችም የእጃቸውን ይሰጣቸዋል።

19. በምዕራብ ያሉት የእግዚአብሔርን ስም ይፈራሉ፤በፀሓይ መውጫ ያሉት ለክብሩ ይገዛሉ፤ የእግዚአብሔር እስትንፋስ እንደ ተቋተ፣እንደ ተከማቸም ጐርፍ ይመጣልና።

ኢሳይያስ 59