ኢሳይያስ 52:1-3 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

1. ጽዮን ሆይ፤ ተነሺ፤ ተነሺ፤ኀይልን ልበሺ፤ቅድስቲቱ ከተማ፤ ኢየሩሳሌም ሆይ!የክብር ልብስሽን ልበሺ፤ያልተገረዘ የረከሰምከእንግዲህ ወደ አንቺ አይገባም።

2. ትቢያሽን አራግፊ፤ኢየሩሳሌም ሆይ፤ ተነሺ በዙፋንሽ ላይ ተቀመጪ፤ምርኮኛዪቱ የጽዮን ልጅ ሆይ፤የዐንገትሽን የእስራት ሰንሰለት አውልቀሽ ጣዪ።

3. እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤“ያለ ዋጋ ተሸጣችሁ ነበር፤ያለ ገንዘብ ትቤዣላችሁ።”

ኢሳይያስ 52