ኢሳይያስ 49:1-4 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

1. እናንት ደሴቶች ስሙኝ፤እናንት በሩቅ ያላችሁ ሕዝቦች ይህን አድምጡ፤በእናቴ ማሕፀን ሳለሁ እግዚአብሔር ጠራኝ፤ከመወለዴ በፊት በስም ጠራኝ።

2. አፌን እንደ ተሳለ ሰይፍ አደረገው፤በእጁ ጥላ ሰወረኝ፤የተወለወለ ፍላጻ አደረገኝ፤በሰገባውም ውስጥ ሸሸገኝ።

3. እርሱም፣ “እስራኤል፤ አንተ ባሪያዬ ነህ፤በአንተ ክብሬን እገልጣለሁ” አለኝ።

4. እኔ ግን፣ “ዐላማ ሳይኖረኝ እንዲሁ ደከምሁ፤ምንም ጥቅም ለሌለውና ለከንቱ ነገር ጒልበቴን ጨረስሁ፤ሆኖም ግን ብድራቴ በእግዚአብሔር እጅ፣ዋጋዬም በአምላኬ ዘንድ ነው” አልሁ።

ኢሳይያስ 49