ኢሳይያስ 46:11-13 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

11. ከምሥራቅ ነጣቂ አሞራ፣ከሩቅ ምድር ዐላማዬን የሚፈጽም ሰው እጠራለሁ።የተናገርሁትን አደርጋለሁ፤ያቀድሁትን እፈጽማለሁ።

12. እናንት እልኸኞች፣ከጽድቅም የራቃችሁ ስሙኝ።

13. ጽድቄን እያመጣሁ ነው፤ሩቅም አይደለም፤ማዳኔም አይዘገይም።ለጽዮን ድነትን፣ለእስራኤል ክብሬን አጐናጽፋለሁ።

ኢሳይያስ 46