ኢሳይያስ 43:8-11 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

8. ዐይን እያላቸው የታወሩትን፣ጆሮ እያላቸው የደነቈሩትን አውጣ።

9. ሕዝብ ሁሉ በአንድነት ይሰብሰብ፤ሰውም ይከማች፤ከእነርሱ አስቀድሞ ይህን የነገረን፣የቀድሞውን ነገር ያወጀልን ማን ነው?ሌሎችን ሰምተው፣ “እውነት ነው” እንዲሉ፣ትክክለኝነታቸውም እንዲረጋገጥ ምስክሮቻቸውን ያቅርቡ።

10. “ታውቁና ታምኑብኝ ዘንድ፣እርሱ እኔ እንደሆንሁ ትረዱ ዘንድ፣እናንተ ምስክሮቼ፣የመረጥሁትም ባሪያዬ ናችሁ” ይላል እግዚአብሔር።“ከእኔ በፊት አምላክ አልተሠራም፤ከእኔም በኋላ አይኖርም።

11. እኔ፣ እኔ እግዚአብሔር ነኝ፤ከእኔም ሌላ የሚያድን የለም።

ኢሳይያስ 43