ኢሳይያስ 38:9-11 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

9. የይሁዳ ንጉሥ ሕዝቅያስ ከሕመሙ ከተፈወሰ በኋላ የጻፈው ጽሕፈት፤

10. እኔ፣ “በዕድሜዬ እኩሌታ፣በሲኦል ደጆች ማለፍ አለብኝን?የቀረውንስ ዘመኔን ልነጠቅ ይገባልን?” አልሁ።

11. እንዲህም አልሁ፤ “ዳግም እግዚአብሔርን፣ እግዚአብሔርን በሕያዋን ምድር አላይም፤ከእንግዲህም የሰውን ዘር አላይም፤በዚህ ዓለም ከሚኖሩትም ጋር አልሆንም።

ኢሳይያስ 38