ኢሳይያስ 3:10-14 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

10. ጻድቃን መልካም ነገር እንደሚያገኙ ንገሯቸው፤የሥራቸውን ፍሬ ይበላሉና።

11. በደለኞች ወዮላቸው፤ ጥፋትይመጣባቸዋል፤የእጃቸውን ያገኛሉና።

12. ወጣቶች ሕዝቤን ያስጨንቃሉ፤ሴቶችም ይገዟቸዋል።ሕዝቤ ሆይ፤ መሪዎችህ አሳስተውሃል፤ከመንገድህም መልሰውሃል።

13. እግዚአብሔር በፍርድ ወንበር ላይ ተቀምጦአል፤በሕዝቡም ላይ ለመፍረድ ተነሥቶአል።

14. እግዚአብሔር፣ከአለቆችና ከሕዝቡ ሽማግሌዎች ጋር እንዲህ ሲል ይፋረዳል፤“የወይኔን ቦታ ያጠፋችሁ እናንተ ናችሁ፤ከድኾች የዘረፋችሁትም በቤታችሁ ይገኛል፤

ኢሳይያስ 3