ኢሳይያስ 28:3-5 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

3. የኤፍሬም ሰካራሞች የመታበያ አክሊል፣በእግር ይረገጣል።

4. በለምለሙ ሸለቆ ዐናት ላይ ጒብ ብላ፣የክብሩ ውበት የሆነች ጠውላጋ አበባ፣ከመከር በፊት እንደ ደረሰች፣ሰውም ድንገት አይቶ እንደሚቀጥፋትወዲያውኑም እንደሚውጣት በለስ ትሆናለች።

5. በዚያን ቀን የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር፣ለተረፈው ሕዝቡ፣የክብር ዘውድ፣የውበትም አክሊል ይሆናል።

ኢሳይያስ 28