ኢሳይያስ 27:12-13 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

12. በዚያ ቀን ከኤፍራጥስ ወንዝ አንሥቶ እስከ ግብፅ ደረቅ ወንዝ፤ እግዚአብሔር እህሉን ይወቃል፤ እናንተም የእስራኤል ልጆች ሆይ፤ አንድ በአንድ ትሰበሰባላችሁ።

13. በዚያ ቀን ታላቅ መለከት ይነፋል፤ በአሦር የጠፉትና በግብፅ የተሰደዱትም መጥተው፣ በተቀደሰው ተራራ በኢየሩሳሌም እግዚአብሔርን ያመልካሉ።

ኢሳይያስ 27