ኢሳይያስ 22:1-3 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

1. ስለ ራእይ ሸለቆ የተነገረ ንግር፤እስቲ ምን ቢጨንቃችሁ ነው፤ሁላችሁም ሰገነት ላይ የወጣችሁት?

2. አንቺ ጫጫታ የሞላብሽ ከተማ፤የውካታና የፈንጠዝያ ከተማ ሆይ፤የተገደሉብሽ በሰይፍ የተሠዉ አይደሉም፤በጦርነትም አልሞቱም።

3. መሪዎችሽ በሙሉ በአንድ ላይ ሸሽተዋል፤ቀስት እንኳ ሳያነሡ ተማርከዋል፤ጠላት ገና በሩቅ ሳለ የሸሻችሁ ሁሉ፣ተይዛችሁ በአንድነት ታስራችኋል።

ኢሳይያስ 22