8. ጠባቂው ጮኸ፤ እንዲህም አለ፤“ጌታ ሆይ፤ በየቀኑ ማማ ላይ ቆሜአለሁ፤በየሌሊቱም በቦታዬ አለሁ።
9. እነሆ፤ አንድ ሰው በፈረሶች በሚሳብበሠረገላ መጥቶአል፤እንዲህም ሲል መለሰ፣‘ባቢሎን ወደቀች፣ ወደቀየአማልክቷም ምስሎች ሁሉ፣ተሰባብረው ምድር ላይ ወደቁ።’ ”
10. በዐውድማ ላይ የተወቃህ ሕዝቤ ሆይ፤ከሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር፣ከእስራኤል አምላክ፣የሰማሁትን እነግርሃለሁ።
11. ስለ ኤዶም የተነገረ ንግር፤አንዱ ከሴይር ጠርቶኝ፣“ጠባቂ ሆይ፤ ሊነጋ ምን ያህል ቀረው?ጠባቂ ሆይ፤ ሊነጋ ምን ያህል ቀረው?” አለኝ።