ኢሳይያስ 2:1-3 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

1. የአሞጽ ልጅ ኢሳይያስ ስለ ይሁዳና ስለ ኢየሩሳሌም ያየው ይህ ነው፤

2. በዘመኑም ፍጻሜ፣ የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ተራራከተራሮች ከፍ ብሎ ይመሠረታል፤ከኰረብቶችም በላይ ከፍ ከፍ ይላል፤ሕዝቦችም ሁሉ ወደዚያ ይጐርፋሉ።

3. ብዙ ሕዝቦችም መጥተው እንዲህ ይላሉ፤“ኑ፤ ወደ እግዚአብሔር ተራራ፣ወደ ያዕቆብ አምላክ ቤት እንውጣ፤እርሱ መንገዱን ያስተምረናል፤በጐዳናውም እንሄዳለን።”ሕግ ከጽዮን፣ የእግዚአብሔር ቃል ከኢየሩሳሌም ይወጣልና።

ኢሳይያስ 2