ኢሳይያስ 13:5-9 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

5. እግዚአብሔርና የቍጣው ጦር መሣሪያ፣ምድሪቱን በሙሉ ለማጥፋት፣ከሩቅ አገር፣ከሰማያትም ዳርቻ መጥተዋል።

6. የእግዚአብሔር ቀን ቀርቦአልና አልቅሱ፤ሁሉን ቻይ ከሆነ አምላክ ዘንድ ጥፋት ይመጣልና።

7. ስለዚህ እጆች ሁሉ ሽባ ይሆናሉ፤የሰውም ሁሉ ልብ ይቀልጣል።

8. ሽብር ይይዛቸዋል፤ሥቃይና ጭንቀት ይደርስባቸዋል፤ምጥ እንደ ያዛት ሴት ያምጣሉ፤እርስ በርሳቸው በድንጋጤ ይተያያሉ፤ፊታቸውም በፍርሀት ቀይ ይሆናል።

9. እነሆ፤ የእግዚአብሔር ቀን ጨካኝ ነው፤ምድርን ባድማ ሊያደርጋት፣በውስጧም ያሉትን ኀጢአተኞች ሊያጠፋ፣ከመዓትና ከብርቱ ቍጣ ጋር ይመጣል።

ኢሳይያስ 13