ሰቆቃወ 3:45-50 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

45. በአሕዛብ መካከል፣አተላና ጥራጊ አደረግኸን።

46. “ጠላቶቻችን ሁሉ፣አፋቸውን በእኛ ላይ ከፈቱ።

47. በጥፋትና በመፈራረስ፣በችግርና በሽብር ተሠቃየን።

48. የእንባ ጐርፍ ከዐይኔ ፈሰሰ፤ሕዝቤ አልቋልና።

49. ያለ ዕረፍት፣ያለ ማቋረጥ ዐይኖቼ እንባ ያፈሳሉ፤

50. እግዚአብሔር ከላይ፣ከሰማይ እስኪያይ ድረስ።

ሰቆቃወ 3