ሰቆቃወ 2:9-12 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

9. በሮቿ ወደ ምድር ሰመጡ፤የብረት መወርወሪያዎቻቸውን ሰባበረ፤ አጠፋቸውም፤ንጉሥዋና መሳፍንቶቿ በአሕዛብ መካከል ተማርከው ተሰደዋል፤ሕጉ ከእንግዲህ አይኖርም፤ነቢያቶቿም ከእንግዲህ፣ ከእግዚአብሔር ራእይ አያገኙም።

10. የጽዮን ሴት ልጅ ሽማግሌዎች፣በምድር ላይ በዝምታ ተቀምጠዋል፤በራሳቸው ላይ ትቢያ ነሰነሱ፤ማቅም ለበሱ፤የኢየሩሳሌም ወጣት ሴቶች፣ራሳቸውን ወደ ምድር ዝቅ አደረጉ።

11. ዐይኔ በለቅሶ ደከመ፤ነፍሴ በውስጤ ተሠቃየች፤ልቤም በሐዘን ፈሰሰች፣በከተማዪቱ መንገዶች ላይ፣ሕዝቤ ተደምስሰዋልና፤ልጆችና ሕፃናት ደክመዋልና።

12. በከተማዪቱ መንገዶች ላይ፣እንደ ቈሰሉ ሰዎች ሲደክሙ፣በእናታቸው ክንድ ላይ፣ነፍሳቸው በመውጣት ላይ ሳለች፣“እንጀራና የወይን ጠጅ የት አለ?”እያሉ እናቶቻቸውን ይጠይቃሉ።

ሰቆቃወ 2