12. በከተማዪቱ መንገዶች ላይ፣እንደ ቈሰሉ ሰዎች ሲደክሙ፣በእናታቸው ክንድ ላይ፣ነፍሳቸው በመውጣት ላይ ሳለች፣“እንጀራና የወይን ጠጅ የት አለ?”እያሉ እናቶቻቸውን ይጠይቃሉ።
13. የኢየሩሳሌም ሴት ልጅ ሆይ፤ ስላንቺ ምን ማለት እችላለሁ?ከምንስ ጋር አወዳድርሻለሁ? ድንግሊቱ የጽዮን ልጅ ሆይ፤አጽናናሽ ዘንድ፣በምን ልመስልሽ እችላለሁ?ቍስልሽ እንደ ባሕር ጥልቅ ነው፤ማንስ ሊፈውስሽ ይችላል?
14. የነቢያቶችሽ ራእይ፣ሐሰትና ከንቱ ነው፤ምርኮኛነትሽን ለማስቀረት፣ኀጢአትሽን አይገልጡም።የሚሰጡሽም የትንቢት ቃል፣የሚያሳስትና ከመንገድ የሚያወጣ ነው።