24. የጠራው ከአይሁድ ወገን ብቻ ሳይሆን ከአሕዛብ ወገን የሆነውን እኛን እንኳ ሳይቀር አይደለምን?
25. በሆሴዕ እንዲህ እንደሚል፤“ሕዝቤ ያልሆኑትን፣ ‘ሕዝቤ’ ብዬ እጠራቸዋለሁ”፤ያልተወደደችውንም ‘የተወደደችው’ ብዬ እጠራለሁ።
26. ደግሞም፣ “ ‘ሕዝቤ አይደላችሁም’፤ተብሎ በተነገራቸው በዚያ ቦታ፣‘የሕያው እግዚአብሔር ልጆች’ ተብለውይጠራሉ።”
27. ኢሳይያስም ስለ እስራኤል እንዲህ ሲል ይጮኻል፤“የእስራኤል ልጆች ቊጥር በባሕር ዳር እንዳለ አሸዋ ቢሆንም፣ትሩፉ ብቻ ይድናል።