12. በታላቅ ድምፅም እንዲህ ብለው ዘመሩ፤“የታረደው በግ ኀይልና ባለጠግነት፣ጥበብና ብርታት፣ክብርና ሞገስ፣ ምስጋናም፣ሊቀበል ይገባዋል።
13. ከዚያም በሰማይና በምድር፣ ከምድር በታችና በባሕር፣ በእነርሱ ውስጥ ያሉ ፍጡራንም ሁሉ እንዲህ ብለው ሲዘምሩ ሰማሁ፤“በዙፋኑ ላይ ለተቀመጠውና ለበጉ፣ምስጋናና ሞገስ፣ ክብርና ኀይል፣ከዘላለም እስከ ዘላለም ይሁን።”
14. አራቱ ሕያዋን ፍጡራንም፣ “አሜን” አሉ፤ ሽማግሌዎቹም በግምባራቸው ተደፍተው ሰገዱ።