ምሳሌ 9:5-8 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

5. “ኑ፤ ምግቤን ተመገቡ፤የጠመቅሁትንም የወይን ጠጅ ጠጡ።

6. የሞኝነት መንገዳችሁን ተዉ፤ በሕይወት ትኖራላችሁ፤በማስተዋልም መንገድ ተመላለሱ።

7. “ፌዘኛን የሚገሥጽ ሁሉ ስድብን በራሱ ላይ ያመጣል፤ክፉውን ሰው የሚዘልፍ ሁሉ ውርደት ያገኘዋል።

8. ፌዘኛን አትዝለፈው፤ ይጠላሃል፤ጠቢብን ገሥጸው፤ ይወድሃል።

ምሳሌ 9