ምሳሌ 8:11-15 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

11. ጥበብ ከቀይ ዕንቍ ይበልጥ ውድ ናትና፤ከምትመኙት ነገር ሁሉ አንዳች የሚስተካከላት የለም።

12. “እኔ ጥበብ ከማስተዋል ጋር አብሬ እኖራለሁ፤ዕውቀትና ልባምነት ገንዘቦቼ ናቸው።

13. እግዚአብሔርን መፍራት ክፋትን መጥላት ነው፤እኔም ትዕቢትንና እብሪትን፣ክፉ ጠባይንና ጠማማ ንግግርን እጠላለሁ።

14. ምክርና ትክክለኛ ፍርድ የእኔ ናቸው፤ማስተዋል አለኝ፤ ብርታት አለኝ።

15. ነገሥታት በእኔ ይነግሣሉ፤ገዦችም ትክክል የሆነውን ሕግ ይደነግጋሉ፤

ምሳሌ 8