ምሳሌ 7:8-12 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

8. የቤቷን አቅጣጫ ይዞ፣በቤቷ ማእዘን አጠገብ ባለው መንገድ ያልፍ ነበር፤

9. ቀኑ መሸትሸት ሲል፣በውድቅት ሌሊት፣ በጽኑ ጨለማ።

10. ከዚያም አንዲት ሴት ልታገኘው ወጣች፤እንደ ዝሙት አዳሪ ለብሳ፣ ለማሳሳት ታጥቃ።

11. ጯኺና ማን አለብኝ ባይ ናት፤እግሮቿ አርፈው ቤት አይቀመጡም፤

12. አንዴ በመንገድ፣ አንዴ በአደባባይ፤በየማእዘኑም ታደባለች።

ምሳሌ 7