ምሳሌ 7:4-9 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

4. ጥበብን፣ “እኅቴ ነሽ” በላት፤ማስተዋልንም፣ “ዘመዴ ነህ” በለው፤

5. ከአመንዝራ ሴት፣በአንደበቷም ከምታታልል ዘልዛላ ሴት ይጠብቁሃል።

6. በቤቴ መስኮት፣በዐይነ ርግቡ ወደ ውጭ ተመለከትሁ።

7. ማስተዋል የጐደለውን ወጣት፣ብስለት ከሌላቸው መካከል አየሁት፤ከጎልማሶችም መካከል ለየሁት።

8. የቤቷን አቅጣጫ ይዞ፣በቤቷ ማእዘን አጠገብ ባለው መንገድ ያልፍ ነበር፤

9. ቀኑ መሸትሸት ሲል፣በውድቅት ሌሊት፣ በጽኑ ጨለማ።

ምሳሌ 7