ምሳሌ 6:25-29 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

25. ውበቷን በልብህ አትመኝ፤በዐይኗም አትጠመድ፤

26. ጋለሞታ ሴት ቊራሽ እንጀራ ታሳጣሃለችና፤አመንዝራዪቱም በሕይወትህ በራሱ ላይ ትሸምቃለች።

27. ለመሆኑ ልብሱ ሳይቃጠል፣በጒያው እሳት መያዝ የሚችል ሰው አለን?

28. አንድ ሰው እግሮቹ ሳይቃጠሉ፣በፍም ላይ መሄድ ይችላልን?

29. ከሰው ሚስት ጋር የሚተኛም እንደዚሁ ነው፤የሚደርስባትም ከቅጣት አያመልጥም።

ምሳሌ 6