ምሳሌ 5:6-10 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

6. ስለ ሕይወት መንገድ ደንታ የላትም፤መንገዶቿ ዘወርዋራ ናቸው፤ ለእርሷ ግን አይታወቃትም።

7. እንግዲህ፣ ልጆቼ ሆይ፤ አድምጡኝ፤ከምነግራችሁ ቃል ፈቀቅ አትበሉ።

8. መንገድህን ከእርሷ አርቅ፤በደጃፏም አትለፍ፤

9. ይኸውም ጒብዝናህን ለሌሎች፣ዕድሜህንም ለጨካኞች እንዳትሰጥ ነው፤

10. ባዕዳን በሀብትህ እንዳይፈነጥዙ፣ልፋትህም የሌላውን ሰው ቤት እንዳያበለጽግ ነው።

ምሳሌ 5