ምሳሌ 4:17-20 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

17. የክፋት እንጀራ ይበላሉ፤የዐመፅ ወይን ጠጅ ይጠጣሉ።

18. የጻድቃን መንገድ ሙሉ ቀን እስኪሆን ድረስ፣ብርሃኑ እየጐላ እንደሚሄድ የማለዳ ውጋጋን ነው።

19. የክፉዎች መንገድ ግን እንደ ድቅድቅ ጨለማ ነው፤ምን እንደሚያሰናክላቸውም አያውቁም።

20. ልጄ ሆይ፤ የምነግርህን አስተውል፤ቃሌንም በጥንቃቄ አድምጥ።

ምሳሌ 4