ምሳሌ 31:10-14 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

10. ጠባየ መልካምን ሚስት ማን ያገኛታል?ከቀይ ዕንቊ እጅግ ትበልጣለች።

11. ባሏ ሙሉ በሙሉ ይተማመንባታል፤የሚጐድልበትም ነገር የለም።

12. በሕይወት ዘመኗ ሁሉ፣መልካም ታደርግለታለች እንጂ አትጐዳውም።

13. የበግ ጠጒርና የተልባ እግር መርጣ፣ሥራ በሚወዱ እጆቿ ትፈትላቸዋለች።

14. እንደ ንግድ መርከብ፣ምግቧን ከሩቅ ትሰበስባለች።

ምሳሌ 31