ምሳሌ 3:5-8 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

5. በፍጹም ልብህ በእግዚአብሔር ታመን፤በራስህ ማስተዋል አትደገፍ፤

6. በመንገድህ ሁሉ እርሱን ዕወቅ፤እርሱም ጐዳናህን ቀና ያደርገዋል።

7. በራስህ አስተያየት ጠቢብ ነኝ አትበል፤ እግዚአብሔርን ፍራ፤ ከክፉም ራቅ።

8. ይህም ለሰውነትህ ጤንነትን፣ለዐጥንትህም ልምላሜን ያመጣልሃል።

ምሳሌ 3