ምሳሌ 29:19-23 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

19. አገልጋይ በቃል ብቻ ሊታረም አይችልም፤ቢያስተውለውም እንኳ በጀ አይልም።

20. በችኰላ የሚናገርን ሰው ታያለህን?ከእርሱ ይልቅ ተላላ ተስፋ አለው።

21. ሰው አገልጋዩን ከልጅነቱ ጀምሮ ቢያቀማጥል፣የኋላ ኋላ ሐዘን ያገኘዋል።

22. ቊጡ ሰው ጠብን ይጭራል፤ግልፍተኛም ብዙ ኀጢአት ይሠራል።

23. ሰውን ትዕቢቱ ያዋርደዋል፤ ትሑት መንፈስ ያለው ግን ክብርንይጐናጸፋል።

ምሳሌ 29