ምሳሌ 27:20-22 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

20. ሲኦልና የሙታን ዓለም እንደማይጠግቡ ሁሉ፣የሰውም ዐይን አይረካም።

21. ብር በማቅለጫ፣ ወርቅ በከውር እንደሚፈተን፣ሰውም በሚቀበለው ምስጋና ይፈተናል።

22. ጅልን በሙቀጫ ብትወቅጠው፣እንደ እህልም በዘነዘና ብታደቀው፣ጅልነቱን ልታስወግድለት አትችልም።

ምሳሌ 27