ምሳሌ 25:23-25 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

23. የሰሜን ነፋስ ዝናብ እንደሚያመጣ ሁሉ፣ሐሜተኛ ምላስም ቊጡ ፊት ታስከትላለች።

24. ከጨቅጫቃ ሚስት ጋር በአንድ ቤት ከመኖር፣በጣራ ማእዘን ላይ መኖር ይሻላል።

25. ከሩቅ የሚመጣ መልካም ዜና፣የተጠማችን ነፍስ እንደሚያረካ ቀዝቃዛ ውሃ ነው።

ምሳሌ 25