ምሳሌ 2:3-6 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

3. እንዲሁም የመለየት ጥበብን ብትማጠን፣ድምፅህን ከፍ አድርገህ ማስተዋልን ብትጣራ፣

4. እርሷንም እንደ ብር ብትፈልጋት፣እንደ ተሸሸገ ሀብት አጥብቀህ ብትሻት፣

5. በዚያን ጊዜ ፈሪሀ እግዚአብሔርን ትረዳለህ፤አምላክንም ማወቅ ታገኛለህ።

6. እግዚአብሔር ጥበብን ይሰጣልና፤ከአንደበቱም ዕውቀትና ማስተዋል ይወጣል።

ምሳሌ 2