ምሳሌ 19:14-17 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

14. ቤትና ሀብት ከወላጆች ይወረሳሉ፤አስተዋይ ሚስት ግን ከእግዚአብሔር ዘንድ ናት።

15. ስንፍና ከባድ እንቅልፍ ላይ ይጥላል፤ዋልጌም ሰው ይራባል።

16. ትእዛዛትን የሚያከብር ሕይወቱን ይጠብቃል፤መንገዱን የሚንቅ ግን ይሞታል።

17. ለድኻ የሚራራ ለእግዚአብሔር ያበድራል፤ስላደረገውም ተግባር ዋጋ ይከፍለዋል።

ምሳሌ 19