ምሳሌ 18:3-7 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

3. ክፋት ስትመጣ ንቀት ትከተላለች፤ከዕፍረትም ጋር ውርደት ትመጣለች።

4. ከሰው አፍ የሚወጡ ቃላት ጥልቅ ውሆች ናቸው፤የጥበብም ምንጭ እንደሚንዶለዶል ፏፏቴ ነው።

5. ለክፉ ሰው ማድላት፣ንጹሑንም ፍትሕ መንሣት ተገቢ አይደለም።

6. የተላላ ከንፈር ጠብ ያመጣበታል፤አፉም በትር ይጋብዛል።

7. ተላላ ሰው አፉ መጥፊያው ነው፤ከንፈሮቹም ለነፍሱ ወጥመድ ናቸው።

ምሳሌ 18