ምሳሌ 17:23-26 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

23. ክፉ ሰው ፍትሕ ለማዛባት፣በስውር ጒቦ ይቀበላል።

24. አስተዋይ ሰው ጥበብን ከፊቱ አይለያትም፤የተላሎች ዐይኖች ግን እስከ ምድር ዳርቻ ይንከራተታሉ።

25. ተላላ ልጅ በአባቱ ላይ ሐዘን ያስከትላል፤ለወለደችውም ምሬት ይሆንባታል።

26. ንጹሑን ሰው መቅጣት ተገቢ አይደለም፤ሹሞችን ስለ ቅንነታቸው መግረፍ መልካም አይደለም።

ምሳሌ 17