ምሳሌ 15:28-30 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

28. የጻድቅ ሰው ልብ የሚሰጠውን መልስ ያመዛዝናል፤የክፉ ሰው አፍ ግን ክፋትን ያጐርፋል።

29. እግዚአብሔር ከክፉዎች ሩቅ ነው፤የጻድቃንን ጸሎት ግን ይሰማል።

30. ብሩህ ገጽታ ልብን ደስ ያሰኛል፤መልካም ዜናም ዐጥንትን ያለመልማል።

ምሳሌ 15