ምሳሌ 13:11-15 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

11. ያላግባብ የተገኘ ገንዘብ እየተመናመነ ያልቃል፤ገንዘቡን ጥቂት በጥቂት የሚያከማች ግን ይጠራቀምለታል።

12. ለነገ የሚባል ተስፋ ልብን ያሳምማል፤የተሳካ ምኞት ግን የሕይወት ዛፍ ነው።

13. ምክርን የሚያቃልል በራሱ ላይ ጥፋት ያመጣል፤ትእዛዝን የሚያከብር ግን ወሮታን ይቀበላል።

14. የጠቢብ ትምህርት የሕይወት ምንጭ ናት፤ሰውን በሞት ወጥመድ እንዳይያዝ ታደርገዋለች።

15. መልካም ማስተዋል ሞገስን ታስገኛለች፤የከዳተኞች መንገድ ግን አስቸጋሪ ነው።

ምሳሌ 13