ምሳሌ 10:20-24 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

20. የጻድቅ አንደበት የነጠረ ብር ነው፤የክፉ ሰው ልብ ግን ርባና የለውም።

21. የጻድቃን ከንፈሮች ብዙዎችን ያንጻሉ፤ተላሎች ግን ከማመዛዘን ጒድለት ይሞታሉ።

22. የእግዚአብሔር በረከት ብልጽግናን ታመጣለች፤መከራንም አያክልባትም።

23. ተላላ ሰው በክፉ ተግባር ይደሰታል፤አስተዋይ ሰው ግን በጥበብ ደስ ይለዋል።

24. ክፉ ሰው የፈራው ይደርስበታል፤ጻድቅ የሚመኘው ይፈጸምለታል።

ምሳሌ 10