ምሳሌ 1:20-23 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

20. ጥበብ በጐዳና ላይ ጮኻ ትጣራለች፤በየአደባባዩ ድምፅዋን ከፍ ታደርጋለች፤

21. ዉካታ በበዛባቸው ጐዳናዎች ላይ ትጮኻለች፤በከተማዪቱም መግቢያ በር ላይ እንዲህ ትላለች፤

22. “እናንት ብስለት የሌላችሁ ማስተዋል የሌለበት መንገዳችሁን እስከ መቼ ትወዱታላችሁ?ፌዘኞች በፌዝ ደስ የሚሰኙት፣ሞኞችስ ዕውቀትን የሚጠሉት እስከ መቼ ነው?

23. ዘለፋዬን ብትሰሙኝ ኖሮ፣ልቤን ባፈሰስሁላችሁ፣ሐሳቤንም ባሳወቅኋችሁ ነበር።

ምሳሌ 1