ማርቆስ 7:6-10 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

6. እርሱም እንዲህ ሲል መለሰ፤ “ኢሳይያስ ስለ እናንተ፣ ስለ ግብዞች በትክክል ተንብዮአል፤ እንዲህ ተብሎ ተጽፎአልና፤ “ ‘ይህ ሕዝብ በከንፈሩ ያከብረኛል፤ ልቡ ግን ከእኔ የራቀ ነው፤

7. በከንቱ ያመልከኛል፤ ትምህርታቸውም ሰው ሠራሽ ሥርዐት ብቻ ነው።’

8. የእግዚአብሔርን ትእዝዛዝ ትታችሁ የሰዎችን ወግና ሥርዐት ታጠብቃላችሁ።”

9. ደግሞም፣ እንዲህ አላቸው፤ “የራሳችሁን ወግ ለመጠበቅ ስትሉ፣ የእግዚአብሔርን ትእዛዝ የምትተውበት ዘዴ አላችሁ።

10. ሙሴ፣ ‘አባትህንና እናትህን አክብር፤ አባቱን ወይም እናቱን የሚሳደብ ፈጽሞ ይሙት ብሎ ነበርና፤

ማርቆስ 7