1. በሌላ ጊዜ ደግሞ በባሕሩ አጠገብ ያስተምር ጀመር። እርሱ ባለበት አካባቢ እጅግ ብዙ ሕዝብ ስለ ተሰበሰበ፣ በባሕሩ ላይ ወዳለች ጀልባ ገብቶ ተቀመጠ፤ ሕዝቡም ሁሉ በባሕሩ ዳርቻ ባለው ስፍራ ላይ ተሰብስቦ ነበር።
2. እርሱም ብዙ ነገሮችን በምሳሌ አስተማራቸው፤ እንዲህም አላቸው፤
3. “ስሙ፤ አንድ ዘሪ ዘር ሊዘራ ወጣ።
4. ዘሩን በሚዘራበትም ጊዜ አንዳንዱ መንገድ ላይ ወደቀ፤ ወፎችም መጥተው ለቅመው በሉት።