ማርቆስ 2:22-24 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

22. እንዲሁም አዲስ የወይን ጠጅ በአሮጌ አቍማዳ የሚያስቀምጥ የለም፤ ይህ ከተደረገማ የወይን ጠጁ አቍማዳውን ያፈነዳዋል፤ የወይን ጠጁም አቍማዳውም ይበላሻሉ። ስለዚህ አዲስ የወይን ጠጅ መቀመጥ ያለበት በአዲስ አቍማዳ ነው።”

23. በሰንበት ቀን ኢየሱስ በእርሻ መካከል ሲያልፍ፣ አብረውት በመጓዝ ላይ የነበሩት ደቀ መዛሙርቱ እሸት ይቀጥፉ ጀመር።

24. ፈሪሳውያንም፣ “እነሆ፤ በሰንበት ቀን ለምን የተከለከለ ነገር ያደርጋሉ?” ሲሉ ጠየቁት።

ማርቆስ 2